መሃይምነት ድራማ ክፍል 6 -የእረፍት ግዜ | በማ ድመጥ መማር | DW | 08.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

በማ ድመጥ መማር

መሃይምነት ድራማ ክፍል 6 -የእረፍት ግዜ

በመሃይምንትና በትምህርት ዙሪያ ሴት ልጅ መማር አለባት በሚል ርእስ በተከታታይ የምናቀርበውን ዝግጅት ነው ። የእረፍት ጊዜው ለልእልት በጣም የተሻለ መረጋጋትን ሰጥቷታል፡

የአባቷ አቶ ወልዳይ የንግድ ድርጀትም ወደ ቀድሞ ይዞታው ተመልሷል፡፡ በብረታ ብረት ስራ ድርጅቱ ተቀጣሪ የሆነው ኤፍሬም ከጊዜ ወደ ጊዜ ተሰሚነቱ እየጨመረ ነው፡፡ ምክንያቱም ለማታ ትምህርቱ ምስጋና ይግባውና ድርጅቱ የሚያድግበትን ዘዴዎችን እያፈላለገ ነው፡፡ አውሮፓውያኑ አገር ጎብኚዎችን የአቶ ወልዳይ የእጅ ስራ ውጤት በሆኑት ምርቶች ላይ ቅሬታ አላቀረቡም፡፡ ስለሆነም ነገሮች እየተሻሻሉ በመሄዳቸው አቶ ወልዳይ ባለቤታቸው ወ/ሮ መብራት የተበደሩትን ብድር መክፈል ጀምረዋል፡፡ ሕይወት ብሩህ ሆናለች፡፡ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ልእልት ከጓደኛዋ ዙሪያሽ አገር ጎብኚዎች ጋር አብራቸው እንድትሔድ ተፈቅዶላት፡፡ አሁን የምሳ ሰአት ስለሆነ በአንድ ተራራው አካባቢ በጋራ ምሳቸውን እየበሉ ነው፡፡ ክፍል 6 ጭውውት ይቀጥላል፡፡