ሐራሬ-የአፍቃ ሕብረት ጥሪና የዚምባቡዌዎች መልስ | ዜና | DW | 03.07.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዜና

ሐራሬ-የአፍቃ ሕብረት ጥሪና የዚምባቡዌዎች መልስ

ሐራሬ-የአፍቃ ሕብረት ጥሪና የዚምባቡዌዎች መልስ

የዚምባቡዌ መንግሥትና ዋነኛዉ ተዋቂ ፓርቲ ተጣሪ መንግሥት ለመመስረት እንዲደራደሩ የአፍሪቃ ሕብረት ያደረገዉን ጥሪ በየፊናቸዉ ተቀበሉት።ሻርም-አልሼክ ግብፅ ዉስጥ ተሰብስበዉ የነበሩት የአፊቃ መሪዎች ለፕሬዝዳት ሮበርት ሙጋቤ እዉቅና መንፈግን ጨምሮ በዚምባቡዌዉ መንግሥት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ምዕራቡዉያን ሐገራት ግፊት ሲያደርጉ ነበር።ጉባኤተኞቹ ግን የዚምባቡዌ ተቀናቃኝ ሐይላት እንዲደራደሩ ከመጠየቅ ባለፍ የምዕራባዉያኑን ግፊት አልተቀበሉትም።የደቡባዊ አፍሪቃ የጋራ ልማት ማሕበረሰብን ወክለዉ የዚምባቡዌ ፖለቲከኞችን እስካሁን ሲያደራድሩ የነበሩት የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳት ታቦ ኢምቤኪ እንዳሉት ጉባኤተኞች ዚምባቡዌዎች ማድረግ ያለባቸዉንና የሌለባቸዉ ማዘዝ አይችሉም።

«እኛ በርግጠኝነት፥ በርግጥኝነት የአፍሪቃ ክፍለ-አለም፥ ዚምባቡዌዎች ራሳቸዉ ሥለሚያደርጉት ዉጤት የሐኪምን የመሥለ ትዕዛዝ ለመስጠት አትችልም።ዚምባቡዌዎች ሐገራችን ዚምባቡዌን ወደፊት ለማራመድ ተወያይተናል፣ ተደራድረናል፥ በዚሕ ጉዳይ ነዉ-የተስማማነዉ ሲሉ ልንተባበራቸዉ ግድ ነዉ።


የዚምባቡዌ ማስታወቂያ ሚንስትር ሲኻንዪሱ ንድሎቮ ዛሬ እንዳሉት መንግሥታቸዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጥያቄን ይቀበለዋል።ንቅናቄ ለዲሞክራሲያዊ ለዉጥ MDC በምሕፃሩ ከተሰኘዉ ከዋነኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎችም ተቃዋሚዎች ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነዉ።ተቃዋሚዉ ፓርቲ ግን የአፍሪቃ ሕብረትን ጥሪ በከፊል ነዉ የተቀበለዉ።

አንድ የፓርቲዉ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንዳሉት ድርድሩ ተጣማሪ መንግሥት ለመመስረት ከሆነ ፓርቲያቸዉ በድድሩ አይካፈልም።

«የብሔራዊ አንድነት መንግሥትን በሚመለከዉ ጉዳይ የዚሕ አካል እንደማንሆን ግልፅ ማድረግ እፈልጋለሁ።የሽግግር አስተዳደርን በተመለከተ ግን አዎ! ከዚሕ ግብ ለመድረስ ዝግጁ ነዉ።»

አንዳድ የፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚሉት የዚምባቡዌን ዉዝግብ ለመፍታት ተጣማሪ መንግሥት ከመመስረቱ አማራጭ የሚሻል አይኖርም።የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙንም የኬንያን አይነት መፍትሔ ጠቁመዋል።