ለ3 ኤርትራውያን ጋዜጠኖች ሽልማት መሰጠቱ | አፍሪቃ | DW | 05.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ለ3 ኤርትራውያን ጋዜጠኖች ሽልማት መሰጠቱ

ጋዜጠኞቹ በኤርትራ ከሚደርስባቸው ጫና በመሸሽ በተሰደዱበት ኡጋንዳ በጀመሩት United Hearts በተባለ ድረ ገፃቸው ጠንካራ ዘገባዎች በማቅረባቸውና ቡና ልዩ ልዩ ሃሳቦችንም በነፃነት በማስተናገዳቸው ለሽልማት በቅተዋል ።


ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ መብት የቆመው የካናዳ የጋዜጠኞች ድርጅት የ2013 ዓለም ዓቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ለ3 ኤርትራውያንና ለአንድ የቱርክ ጋዜጠኛ ሸልሟል ። 3ቱ ጋዜጠኞች ደሳለኝ በረከት ፣ መብራቱ ተክለ ጽዮንና ሩት ዘካርያስ ኤርትራው ውስጥ በጋዜጠኝነት ይሰሩ ነበር ። ጋዜጠኞቹ በኤርትራ ከሚደርስባቸው ጫና በመሸሽ በተሰደዱበት ኡጋንዳ በጀመሩት United Hearts በተባለ ድረ ገፃቸው ጠንካራ ዘገባዎች መማቅረባቸውና ልዩ ልዩ ሃሳቦችንም በነፃነት በማስተናገዳቸው ለሽልማት መብቃታቸውን ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ዘግባለች ።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic