ለትንበያ ያስቸገረው የብሪታኒያ ምርጫ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ለትንበያ ያስቸገረው የብሪታኒያ ምርጫ

የነገው አጠቃላይ ምርጫ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አስቸጋሪ ሆኗል ። በአሁኑ ምርጫ እስከዛሬ ብዙም ድጋፍ ያልነበራቸው ፓርቲዎች የተሻለ ድምጽ ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ነገ በመላ ብሪታኒያ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ የመጨረሻ የምርጫ ዘመቻቸውን አካሂደዋል ።ባለፉት 5 ሳምንታት በተካሄዱት የምርጫ ዘመቻዎች ከዋነኛዎቹ ተፎካካሪዎች ከወግ አጥባቂው ፓርቲ እጩ ዴቪድ ኬምረንም ሆነ ከሌበር ፓርቲው ተወዳዳሪ ኤድ ሚሊባንድ ማንኛቸው የመሪነቱን ቦታ ሊይዙ እንደሚችል ግልፅ አልነበረም ። በዚህ የተነሳም የነገው አጠቃላይ ምርጫ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አስቸጋሪ ሆኗል ። በአሁኑ ምርጫ እስከዛሬ ብዙም ድጋፍ ያልነበራቸው ፓርቲዎች የተሻለ ድምጽ ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ስለ ነገው የብሪታኒያ አጠቃላይ ምርጫ የለንደኑን ዘጋቢያችንን ድል ነሳ ጌታነህን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ድል ነሳ ጌታነህ

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic