ለሩሲያ ጥቃት IS ተጠያቂ ሆነ ፤ የፊላንድ እየተጣራ ነው | ዓለም | DW | 19.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ለሩሲያ ጥቃት IS ተጠያቂ ሆነ ፤ የፊላንድ እየተጣራ ነው

ራሱን እስላማዊ መንግሥት እያለ የሚጠራው ቡድን ዛሬ በሩሲያ ሱርጉት ከተማ በስለት ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት ወሰደ። በሌላ ዜና ፊንላንድ ውስጥ ሁለት ሰዎች ዓርብ ዕለት በስለት ከተገደሉ በኋላ ፖሊስ የሽብር ጥቃት መሆኑን እያጣራ ይገኛል።

ራሱን እስላማዊ መንግሥት እያለ የሚጠራው ቡድን ዛሬ በሩሲያ ሱርጉት ከተማ ለደረሰው ጥቃት፤  ፈፃሚው «የቡድናችን አባል» ነው ሲል ቡድኑ አማቅ በተሰኘ የዜና አገልግሎት በኩል አስታውቋል። ቡድኑ በርግጥ ከጥቃቱ ጀርባ መኖሩ በይፋ አልተረጋገጥም።  መረጃውን ያወጣው አማቅ የዜና አገልግሎት ቡድኑ ከዚህ ቀደም መልዕክቶችን ያሰራጭበት የነበረ ነው ተብሏል። በዛሬው የሱርጉት ከተማ ጥቃት አንድ ጥቃት ፈፃሚ በእግረኞች ጎዳና ላይ ሰባት ሰዎችን በስለት ወግቶ አቁስሏል።

Karte Finnland Turku ENG

ፊንላንድ ቱርኩ ከተማ ሁለት ሰዎች በስለት ተወግተው ሲገደሉ ሌሎች ስምንት ደግሞ ቆስለዋል።

ተጠርጣሪው ወዲያው በፖሊስ መገደሉ ተዘግቧል። የሩሲያ ባለስልጣናት ጥቃት ፈፃሚው ሩሲያዊ ስለሆነ የሽብር ጥቃት መሆኑን አስተባብለው ነበር። 

በሌላ ዜና ፊንላንድ ውስጥ ሁለት ሰዎች ዓርብ ዕለት በስለት ከተገደሉ በኋላ ፖሊስ የሽብር ጥቃት መሆኑን እያጣራ ይገኛል። ፖሊስ ሌሊቱን ባካፌደው ምርመራ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ የሽብር ጥቃትን የሚጠቁም መረጃ ማግኘቱን አሳውቋል። እስካሁን ከጥቃት ፈፃሚው ጋር ግንኙነት ይኖራቸዋል የተባሉ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ተጠርጣሪው የ 18 ዓመት ሞሮኩዋዊ  ሲሆን፤ ፖሊስ እግሩ ላይ በጥይት መቶ ጥቃቱን ማስቆሙን ገልጿል። በዚህ ጥቃት ቱርኩ ከተማ ውስጥ በጠቅላላው ሁለት ሰዎች በስለት ተወግተው ሲገደሉ ሌሎች ስምንት ደግሞ ቆስለዋል።

ልደት አበበ

ተስፋለም ወልደየስ