1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፓሪስ ጥቃቷን እያሰበች ዋለች

ሰኞ፣ ኅዳር 4 2010

ዛሬም በጥብቅ ማስጠንቀቂያ ውስጥ የምትገኘው የፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ከሁለት አመት በፊት በአጥፍቶ ጠፊዎች እና ታጣቂዎች 130 ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት ስታስብ ውላለች።

https://p.dw.com/p/2nYJl
Frankreich zweiter Jahrestag der Anschläge in Paris
ምስል Reuters/E. Laurent

ፓሪስ ከሁለት አመት በኋላ

ጥቃቱ በተፈጸመባቸው ስድስት ቦታዎች ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ በተገኙበት የመታሰቢያ ጉንጉን አበባ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ተካሒዷል። መንግሥታቸው መሰል ጥቃቶችን ለመከላከል  ለፖሊስ እና የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች የስልክ ንግግሮችን የመጥለፍ፣ የመበርበር እና የማሰር ሰፊ ስልጣን የሰጠው ኤማኑዌል ማክሮ በመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓቱ ሌሎች ከፍተኛ ሹማምንትም አጅበዋቸዋል። ከሁለት አመት በፊት ለተፈጸመው ጥቃት ራሱን "እስላማዊ መንግሥት" ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ኃላፊነት ወስዷል። ፓሪስ ከአመት በኋላ ምን ትመስል ይሆን? ሐይማኖት ጥሩነህ የፓሪስ ነዋሪዎችን አነጋግራ የሚከተለውን ዘገባ ልካልናለች። 
ሐይማኖት ጥሩነህ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ