1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፍራንክፈርት-የጀርመን እና የኢትዮጵያ ባለሐብቶች ዉይይት

ዓርብ፣ ነሐሴ 25 2010

የጀርመን ባለሐብቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ የመወረት ፍላጎታቸዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የሁለቱ ሐገራት ባለሥልጣናት እና ባለሐብቶች አስታወቁ።ዛሬ ፍራንክፍረት ጀርመን ዉስጥ ሥለ ሁለቱ ሐገራት ምጣኔ ሐብታዊ ግንኙነት የመከረዉ ስብሰባ ተካፋዮች እንዳሉት የጀርመን ባለሐብቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚወርቱባቸዉ በርካታ መስኮች እና ዕድሎች አሉ።

https://p.dw.com/p/347kR
Detuschland Äthiopisch-Deutsches Wirtschaftsforum beim äthiopischen Konsulat in Frankfurt
ምስል Äthiopisches Generalkonsulat in Frankfurt

የኢትዮጵያ እና የጀርመን የምጣኔ ሐብት መድረክ

የጀርመን ባለሐብቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ የመወረት ፍላጎታቸዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የሁለቱ ሐገራት ባለሥልጣናት እና ባለሐብቶች አስታወቁ።ዛሬ ፍራንክፍረት ጀርመን ዉስጥ ሥለ ሁለቱ ሐገራት ምጣኔ ሐብታዊ ግንኙነት የመከረዉ ስብሰባ ተካፋዮች እንዳሉት የጀርመን ባለሐብቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚወርቱባቸዉ በርካታ መስኮች እና ዕድሎች አሉ።በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ኩማ ደመቅሳ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠራቸዉን ኩባንዮች ለግል ባለሐብቶች ለመሸጥ በቅርቡ መወሰኑ የጀርመን ባለሐብቶችን ካማለሉ እርምጃዎች አንዱ ነዉ።አቶ ኩማ አክለዉ እንዳሉት አፍሪቃ ባጠቃላይ፤ ኢትዮጵያ በተለይ ወረታቸዉን ለማፍሰስ ሲያቅማሙ የነበሩት የጀርመን ባለሐብቶች አስተሳሰብ አሁን እየተቀየረ ነዉ።«የኢትዮጵያ እና የጀርመን የምጣኔ ሐብት መድረክ» በተባለዉ በዛሬዉ ስብሰባ ላይ የተካፈሉት የኢንቨስትመንት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተካ ገብረየሱስ በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ ለባለሐብቶች ምቹ መሆንዋን መስካሪዎቹ እራሳቸዉ ጀርመኖች ናቸዉ ይላሉ።ዛሬ ዉለዉን በተደረገዉ ስብሰባ የኢትዮጵያ እና የጀርመንን የምጣኔ ሐብት ትስስር የቃኙ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ