የስደተኞቹ ዕጣ
ሐሙስ፣ ሰኔ 28 2010ማስታወቂያ
አኳሪየስ እና ላይፍ ላይን የተባሉ የነብስ አድን ድርጅቶች መርከቦች ከመስመጥ አደጋ ካዳኗቸዉ ስደተኞች መካከል ፈረንሳይ ለ132ቱ ጥገኝነት ሰጠች።የፈረንሳይ መንግሥት ከተቀበላቸው ስደተኞች አብዛኞቹ የኤርትራ እና የሱዳን ዜጎች ናቸዉ።ባሕር ዉስጥ ከመስጠም ያዳኗቸዉን ስደተኞች ያሳፈሩት ሁለቱ መርከቦች ኢጣሊያ እና ሞልታ ወደብ እንዳይገቡ የሁለቱ ሐገራት መንግሥታት ከልክለዋቸዉ ለበርካታ ቀናት ባሕር ላይ ሲቀዝፉ ነበር።ኋላ የስጳኝ መንግስት ፈቅዶላቸዉ መርከቦቹ መሕለቃቸዉን ለመጣል ችለዉ ነበር። የፓሪስ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ