1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይ፤ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 22 2011

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የኢማኑኤል ማክሮን ፖለቲካ በመቃወም በሃገሪቱ ዙርያ በተጠራ የተቃዉሞ ሰልፍ በተለይ ፓሪስ ላይ ከፍተጫ ብጥብጥ መነሳቱ ተመለከተ። የፈረንሳይ የሃገር አስተዳደር ሚኒስቴር በፈረንሳይ መዲና ታዋቂ ጎዳና ሻንዜ-ሊዜ ላይ ከ 1000 በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በአጥር የተከለከለ ቦታን ነቃቅለዉ በመግባት ረብሻ ማስነሳታቸዉን ገልፆአል።

https://p.dw.com/p/39GuS
Gelbwesten-Protest in Paris
ምስል AFP/Getty Images/A. Jocard

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የኢማኑኤል ማክሮን ፖለቲካ በመቃወም በሃገሪቱ ዙርያ በተጠራ የተቃዉሞ ሰልፍ በተለይ ፓሪስ ላይ ከፍተጫ ብጥብጥ መነሳቱ ተመለከተ። የፈረንሳይ የሃገር አስተዳደር ሚኒስቴር በፈረንሳይ መዲና ታዋቂ ጎዳና ሻንዜ-ሊዜ ላይ ከ 1000 በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በአጥር የተከለከለ ቦታን ነቃቅለዉ በመግባት ረብሻ ማስነሳታቸዉን ገልፆአል። ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጢስን እና ዉኃን በመርጨት ተጠቅሞአል፤ ከ 100 በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞችንም በቁጥጥር ስር አድርጎአል። በፈረንሳይ ከተሞች ቅጠላማ ቢጫ ሰደርያ ጃኬትን አድርገዉ ተቃዉሞ ለተቃዉሞ ሰልፍ የወጡት ከ 30 ሺህ በላይ ተቃዋሚዎች፤ በሃገሪቱ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉንና ፈረንሳይ በጀመረችዉ የተሃድሶ ለዉጥ ርምጃ አንስማማም ሲሉ ተደምጠዋል። የተቃዉሞ ሰልፉ «ቢጫዉ ሰደርያ» የሜል ስያሜ ተሰጥቶታል። 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ