ፈረንሳይ፣ ተቃዉሞ እና አድማ
ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2011ማስታወቂያ
የፈረንሳይ መንግስት በነዳጅ ዘይት ላይ ያደረገዉን የዋጋ ጭማሪ በመቃወም በተለያዩ ከተሞች የተደረገ እና የሚደረገዉ የአደባባይ ሰልፍ እና አድማ የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት እያሽመደመደዉ ነዉ።«ቢጫ ሰደርያ » የሚባሉት አድመኞች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በገጠሙት ግጭት የሰዉ ሕይወት ጠፍቷል፤ ሐብት ንብረትም ወድሟል። በሕዝባዊዉ ተቃዉሞ አድማ ምክንያት የቀድሞ አቋሙን የለወጠዉ የፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ መንግስት በነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ የተደረገዉን የዋጋ ጭማሪ ለስድስት ወር በሥራ ላይ እንዳይወል አግዷል። የተቃዉሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች ግን ተጨማሪ ተቃዉሞ እንዲደረግ እየጠሩ ነዉ።አንዳድ ፖለቲከኞች ደግሞ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነግግ እየገፋፉ ነዉ።
ኃይማኖት ጥሩነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ