1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በፓሪስ

ሰኞ፣ ጥቅምት 19 2011

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለስራ ጉብኝት ዛሬ ፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ገቡ።  ጠ/ሚንስትሩ በአንድ ቀኑ የፓሪስ ቆይታቸው ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናንተው በሀገሮቻቸው  እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች የጋራ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/37Lpu
Abiy Ahmed  in Paris Emmanuel Macron
ምስል DW/H. Tiruneh

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በፓሪስ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ተር ወርቅነህ ገበየሁን እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን አስከትለው ከቀትር በፊት ፓሪስ የገቡት ጠ/ሚኒስትሩን የፈረንሳይ ባለስልጣናት እና እዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቀብለዋቸዋል። በፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዌል ማክሮ ግብዣ ወደ ፓሪስ የተጓዙት ጠ/ሚ ዐብይ ከሁለቱ ሃገራት ግንኙነት በተጨማሪ የአካባቢውን ሰላም፣ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለውን የማሻሻያ ርምጃ እንዲሁም ንግድ እና የመዋዕለንዋይ ፍሰትን በተመለከተ ከፈረንሳዩ አቻቸው ጋር እንደሚነጋገሩ አቶ ፍፁም አረጋ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በትዊተር ባሰራጩት መረጃ ጠቁመዋል።ጠ/ሚ ፓሪስ በገቡበት ወቀት በፓሪስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኤምባሲ ሠራተኞች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የፓሪስ ወኪላችን ዶክተር ዐቢይን ከተቀበሉት መካከል አንዳንዶቹን አነጋግራለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ