1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ቡሽ በ 94 ዓመታቸዉ አረፉ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 22 2011

የፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከርን  ሞትን የሰሙት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጆርጅ ዳብሊው ቡሽ ትልቁ «የሰዉን ስሜት የሚረዱ የዓለማችን ቀዝቃዛ ጦርነት ያበቁ ታላቅ መሪ ነበሩ» ሲሉ ማወደሳቸዉን ዋሽንግተን የሚገኘዉ ዋይት ሃዉስ ቢሮ አስታዉቋል። ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ጆርጅ ዳብሊው ቡሽ ትልቁ በሚል ስያሜም ይታወቃሉ።  

https://p.dw.com/p/39GpP
Ex-US-Präsdient George H.W. Bush gestorben
ምስል picture alliance/Mark Reinstein/MediaPunch

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ከዚህ ዓለም መለየታቸዉን ተከትሎ ከዓለም ሃገራት መንግሥታትና የመንግሥታት ተጠሪዎች የሐዘን መግለጫ እየላኩ ነዉ። የቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ቡሽ ትናንት ምሽት በተወለዱ በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም መለየታቸዉን በመጀመርያ በትዊተር ያሳወቁት ልጃቸዉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዳብሊዉ ቡሽ ነበሩ። የሟቹ ቡሽ ባለቤት ባርባራ ቡሽ ባለፈዉ ዓመት ሚያዝያ ወር ዉስጥ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ይታወሳል። ከጎርጎረሳዉያኑ 1989 እስከ 1993 ዓም ድረስ የዩናይትድ ስቴትስ 41 ኛ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ያስተዳደሩት ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር በተለይ «ክዌትን ነፃ ማዉጣት» በተሰኘ በተለይ ከኢራቅ ጋር ባካሄዱት ጦርነት ይታወቃሉ። ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር የዩናይትድ ስቴትስ 41 ኛ ፕሬዚዳነት ከመሆናቸዉ ቀደም ሲል ከጎርጎረሳዉያኑ 1981 እስከ 1989 ድረስ ሃገራቸዉን በምክትል ፕሬዚዳንትንትም አገልግለዋል። ፕፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ከምዕራባዉያን መንግሥታት ተጠሪዎች መካከል ለጀርመን ዉኅደት ከፍተኛ ድጋፍ ያሳዩ እና የተዋኅደች ጀርመን ሲሉ በድፍረት የተናገሩ የመጀመርያ ባለሥልጣን ነበሩ። በጀርመን ዉኅደት ዘመን ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር የጀርመኑን የቀድሞ መራሒ መንግሥት ሄልሙት ኮልን ከቀድሞ ሶቭየት ሕብረት ጋር በመሆን ለጀርመን ዉኅደት መቆማቸዉ ይወደሳሉ። የፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከርን  ሞትን የሰሙት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጆርጅ ዳብሊው ቡሽ ትልቁ «የሰዉን ስሜት የሚረዱ የዓለማችን ቀዝቃዛ ጦርነት ያበቁ ታላቅ መሪ ነበሩ» ሲሉ ማወደሳቸዉን ዋሽንግተን የሚገኘዉ ዋይት ሃዉስ ቢሮ አስታዉቋል። ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ጆርጅ ዳብሊው ቡሽ ትልቁ በሚል ስያሜም ይታወቃሉ።  

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ