1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉጥረት የነገሰበት የኬንያ ምርጫ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 16 2010

ኬንያ በዛሬዉ ዕለት በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት በተወሰነዉ መሠረት ድጋሚዉን ምርጫ ግጭት እና ዉጥረት ባጠላበት ድባብ ስታካሂድ ዉላለች። ከዋና ከተማ ናይሮቢ እና የተቃዋሚዉ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች በሚበረክቱባቸዉ አካባቢዎች ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸዉ እና የሰዉ ሕይወትም እንደጠፋ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/2mZBG
Kenia Wahlen - Ausschreitungen in Nairobi
ምስል Reuters/G. Tomasevic

የፖለቲካ ዉጥረቱ ንሯል፤

በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ የምርጫ ቁሳቁሶች ሁሉ እንዳልደረሱ እና ምርጫዉ መስተጓጎሉ ተነግሯል። ካለፈዉ ነሐሴ ወዲህ በምርጫ ዉዝግብ ላይ ስለምትገኘዉ ኬንያ የዛሬ ዉሎ ናይሮቢ የሚገኘዉን ተባባሪ ዘጋቢያችንን ፍቅረማርያም መኮንን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ፍቅረ ማርያም መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ