1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዳግም የኤች አይቪ ተሐዋሲ ስርጭት ስጋት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 11 2009

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤች አይ ቪ ተሐዋሲን ስርጭትን ለመቀነስ የዓለም የጤና ድርጅት እና የሚመለከታቸዉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ አለ። ይህን መሠረት በማድረግም ላለፉት አስርት ዓመታት በሌሎች ሃገራትም ሆነ በኢትዮጵያ የተሐዋሲዉን ስርጭት ለመቀነስ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

https://p.dw.com/p/2gk0I
Lesotho Mobile Gesundheitsversorgung: Bluttests
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kurokawa

ዳግም የኤች አይቪ ተሐዋሲ ስርጭት ስጋት

ኢትዮጵያ ዉስጥ የኤች አይ ቪ ተሐዋሲን ስርጭትን ለመቀነስ በተለያዩ አካላት ርብርብ በተከታታይ ለዓመታት በተደረገዉ ጥረት ከፍተኛ ለዉጥ መመዝገቡን ብዙዎች ያምኑበታል። ካለፉት አራት እና አምስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ምንም እንኳን የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር ቢጨምርም አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ እየተነገረ ነዉ። ለዚህ ምክንያቱም ከምንም በላይ የተገኘዉ ዉጤት ያስከተለዉ መዘናጋት መኖሩን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ያነሳሉ። የዶቼ ቬለ ሳምንታዊ የጤና እና አካባቢ መሰናዶ ሰፋ ያለ ዉይይት በዚህ ላይ አካሂዶ ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት አስደምጧል። ክፍል አንድ ባለፈዉ ሳምንት ቀርቧል። የዉይይቱን ክፍል ሁለት ሙሉ ቅንብር ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ