1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የአሜሪካ እና አዉሮጳ የንግድ ጦርነት

ሐሙስ፣ ግንቦት 23 2010

የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር በብረት እና አልሙንየም ላይ ከጣለዉ አዲስ ቀረጥ ካናዳ፤ ሜክሲኮ እና የአዉሮጳ ሕብረት ለሁለት ወራት ያሕል ምሕረት  እንዲደረግላቸዉ ወስኖ ነበር።የአዉሮጳ ሕብረት እና ሁለቱ መንግሥታት ምሕረቱ ለዘላቂዉ እንዲፀና ዩናይትድ ስቴትስን ሲማፀኑ፤ አፀፋ እርምጃ ለመዉሰድ ሲዝቱም ነበር።

https://p.dw.com/p/2yjSf
UK Sheffield Stahlwerk Symbolbild Strafzölle
ምስል picture-alliance/empics/J. Giles

ዩናይትድ ስቴትስ ከዉጪ በምታስገባዉ ብረት እና አሉሙንየም ምርት ላይ አዲስ የጣለችዉ ግብር ከዛሬ እኩለሌት ጀምሮ ሙሉበሙሉ ይፀናል።የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር በብረት እና አልሙንየም ላይ ከጣለዉ አዲስ ቀረጥ ካናዳ፤ ሜክሲኮ እና የአዉሮጳ ሕብረት ለሁለት ወራት ያሕል ምሕረት  እንዲደረግላቸዉ ወስኖ ነበር።የአዉሮጳ ሕብረት እና ሁለቱ መንግሥታት ምሕረቱ ለዘላቂዉ እንዲፀና ዩናይትድ ስቴትስን ሲማፀኑ፤ አፀፋ እርምጃ ለመዉሰድ ሲዝቱም ነበር።የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ዛሬም በድጋሚ አስጠንቅቀዉ ነበር።«ዉሳኔዉን እስካሁን አናዉቅም፤ይሁንና አዲሶቹ ቀረጦች ከተጣሉ እኛ የአዉሮጳ ሕብረት አባላት ግልፅ አቋም አለን።እርምጃዉ የዓለም ንግድ ድርጅት ደንብን የሚቃረን ነዉ።ሶፊያ ዉስጥ ባደረግነዉ የመጨረሻ ስብሰባችን አዲስ የተጣለዉ ቀረጥ  እኛን እንዳይመለከት ጠይቀናል።አንዳድ  ሐሳቦችን አቅርበናልም።በጋራ እንወስናል።ግን ገና እየጠበቅን ስለሆነ (ዉሳኔያችንን) አሁን አናዉቀዉም»
የዩናይትድ ስቴትሱ የንግድ ሚንስትር ዊበር ሮስ ከጥቂት ሰዓታት በፊት እንዳስታወቁት ግን መስተዳድራቸዉ በብረት እና አልሙኒየም ላይ አዲስ የጨመረዉ ቀረጥ ከዛሬ እኩለሌት ጀምሮ በካናዳ፤ሜክሲኮ እና የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት ላይ ገቢራዊ ይሆናል።የትራምፕ መስተዳድር ከዉጪ በሚገባ ብረት ላይ አዲስ የጣለዉ ቀረጥ 25 ከመቶ ሲሆን፤ አልሙኒየም ላይ ደግሞ 10 በመቶ ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ዦን ክሎድ ዩንከር አሁን ከመሸ እንዳሉት የአዉሮጳ ሕብረት የብቀላ እርምጃ ከመዉሰድ ዉጪ ምርጫ የለዉም።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ