የፍልስጤም ለጋሽ ሐገራት ጉባኤ
ሐሙስ፣ ጥር 24 2010ማስታወቂያ
እስራኤል ከዚሕ ቀደም ከፍልስጤሞች ጋር ባደረገችዉ ዉል መሠረት ከፍልስጤም ጋር ሁለት መንግሥታት ለመመሥረት እንድትደራደር የአዉሮጳ ዲፕሎማቶች እና ፖለቲከኞች እያሳሰቡ ነዉ። ትናንት አካባቢዉን የጎበኙት የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዚግማር ጋብርኤል እንዳሉት የእስራኤል መሪዎች የሁለት መንግሥታት መፍትሔ ከሚለዉ መርሕ ለመራቅ ማቅማማታቸዉ አዉሮጶችን እያሳሰበ ነዉ። ብራስልስ ተሰብሰበዉ የነበሩት የፍልስጤም ለጋሽ ሐገራት ተወካዮችም የፍልስጤም እና የእስራኤልን ዉዝግብ ለማስወገድ አብነቱ የሁለት መንግሥታት «ድርድር ነዉ» ብለዋል። የአዉሮጳ ፖለቲከኞች እና ዲፕሎማቶች መልዕክት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አወዛጋቢዋን የእየሩሳሌም ከተማን የእስራኤል ዋና ከተማ እንደሆነች እዉቅና መስጠታቸዉን በቀጥታ የሚቃረን ነዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ያጠናቀረውን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ