1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ የአስመር ጉብኝትና የሕዝብ አስተያየት 

ሰኞ፣ ሐምሌ 2 2010

የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አሕመድ በተለያዩ የሰላምና የወዳጅነት ግንኙነቶች ላይ የጋራ መግባብያ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

https://p.dw.com/p/316JS
Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል S. Mengist

«ጊዜዉ የመደመር ነዉ፤ ደስ ብሎናል»


በዚህ ስምምነት ኢትዮጵያና ኤርትራ የነበሩበት ጦርነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማብቃቱን በይፋም አዉጀዋል፤ በፊርማቸዉም አፅድቀዋል። ጠ/ሚ ዐብይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ከቀትር በኋላ  አዲስ አበባ ገብተዋል።  ዶቼቬለ ያነጋገርናቸዉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ኤርትራዉያን እና ኢትዮጵያዉያን ወንድማማች ሕዝቦች መሆናቸዉን ኤርትራዉያን አስመስክረዋል። በአስመራ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የተደረገው አቀባበል የእዚህ አንዱ ማሳያ ነዉ ብለዋል።   


ዩሐንስ ገ/እግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ