1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጊብሰን አካደሚ ዳይሬክተር ለመምህራን ወቀሳ የሰጡት ምላሽ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 10 2010

አላግባብ ከስራ ተባረናል ያሉ በአዲስ አበባ የሚገኘው የጊብሰን አካዳሚ ትምህርት ቤት መምህራን  እና  የአዲስ አበባ አጠቃላይ የአዲስ አበባ የትምህርት ጥራት እና ሬጉላተሪ ኤጀንሲ ሰሞኑን በትምህርት ቤቱ ላይ ያሰሙትን ክስ የትምህርት ቤቱ አመራር ሀሰት ሲል አስተባበለ።

https://p.dw.com/p/33Gte
Stadtansicht von Addis Abeba Hauptstadt von Aethiopien
ምስል Imago/photothek

ጊብሰን አካደሚ የገጠመው ውዝግብ

አስሩ ከተለያዩ የትምህርት ቤቱ  ቅርንጫፎች የተባረሩት መምህራን ትምህርት ቤቱ የጥራት ጉድለት የሚታይበት የትምህርት ስርዓት እንደሚከተል እና የሰራተኞችንም መብት እንደማያከብር በግልጽ በመናገራቸው ከስራ ገበታቸው እንደተባረሩ ነው የተናገሩት።  ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር ዛቻ፣ ማስፈራራት እና የደሞዝ ቅጣትም እንደደረሰባቸውም መምህራኑ አስታውቀዋል። ይሁንና፣ የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ አቶ ኡመር አሊ ለዶይቸ ቬለ እንደገለጼት፣  መምህራኑ ከስራ የተባረሩት የዲሲፕሊን ግድፈት በማሳየታቸው  ነው፣ ትምህርት ቤቱም አንዳችም የትምህርት ስርዓት ጥሰት አልፈጸመም። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ