1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን እና ቱርክ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 13 2009

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚግማር ጋብርየል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በምታስረው በቱርክ እያንዳንዱ የጀርመን ዜጋ ተመሳሳይ እጣ ሊገጥመው እንደሚችል ዛሬ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2gu8h
Deutschland Bundesaußenminister Gabriel
ምስል picture-alliance/NurPhoto/E. Contini

MMT_Q&A DL-Türkei Streit - MP3-Stereo

የጀርመን እና የቱርክ ውዝግብ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ጀርመን ወደ ቱርክ የሚጓዙ ዜጎቿ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዛሬ አሳስባለች። የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚግማር ጋብርየል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በምታስረው በቱርክ እያንዳንዱ የጀርመን ዜጋ ተመሳሳይ እጣ ሊገጥመው እንደሚችል ዛሬ ተናግረዋል። ጋብርየል ቱርክ ጀርመናዊ ፔተር ስቶይድነርን እና ሌሎች 5 የመብት ተሟጋቾች ማሰሯ በአንካራ ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ማስከተሉ እንደማይቀር አስጠንቅቀዋል። ስለሁለቱ ሀገራት ውዝግብ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ