1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶክተር አቢይ ምርጫ እና የአውሮጳ ህብረት አስተያየት

ረቡዕ፣ መጋቢት 19 2010

የአውሮጳ ህብረት ገዢው የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ አብዮታዊ ግንባር፣ ኢህአዴግ በጀመረው የለውጥ እና ማሻሻያ መርሀግብሩ ትናንት ዶክተር አቢይ አህመድን አዲሱ የግንባሩ ሊቀመንበር፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ ደመቀ መኮንንን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መመምረጡን አስመልክቶ አስተያየት ሰጠ።

https://p.dw.com/p/2v9YY
Europaflaggen vor dem Hauptquartier der Europäischen Kommission in Brüssel
ምስል Reuters/Y. Herman

የዶክተር አቢይ ምርጫ እና የአውሮጳ ህብረት

ህብረቱ በቃል አቀባዩ በኩል ለዶይቸ ቬለ በጽሑፍ በሰጠው አስተያየት የለውጥ እና ማሻሻያ ፕሮግራም እንደሚቀጥል ተስፋውን ገልጿል። የለውጡ መርሀግብርም የፖለቲካ እስረኞችን መፈታትን እና የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋትን እንደሚያካትትም ቃል አቀባዩ እምነታቸውን አክለው ጠቅሰዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ