የዴሞክራቲክ ኮንጎ የምርጫ ውጤት
ሐሙስ፣ ጥር 2 2011ማስታወቂያ
ዛሬ ይፋ የሆነው የምርጫ ውጤት እንደተፈራው ስልጣን ላይ የሚገኘው ፓርቲ እጩን ሳይሆን የተቃዋሚውን ተፎካካሪ ፌሊክስ ቺሴኬዲ ባለድል መሆናቸውን ቢያውጅም የተፈራው ግጭት ግን የቀረ አይመስልም። ሌላኛው የተቃዋሚ እጩ መፈንቅለ መንግሥት ተደርጎብኛል ማለታቸው ደጋፊዎቻቸውን አደባባይ አውጥቶ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር አጋጭቷል፤ ከፖሊስም ከማርቲን ፋዩሉ ደጋፊዎች ወገንም የተጎዱ መኖራቸው ተነግሯል። የአፍሪቃ ኅብረት ኮንጎ በውጤቱ ተሰበብ የተፈጠረውን ውዝግብ በአግባቡ እንድትፈታ ጠይቋል። ከብራስልስ ገበያው ንጉሤ ዘገባ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ