1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዴምህት የትግል ሥልት

ረቡዕ፣ መስከረም 30 2011

አቶ መኮንን እንደሚሉት ድርጅታቸዉ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ተቀላቅሎ፤ በትብብር ወይም ለብቻዉ መታገል አለመታገሉን በቅርቡ በሚያደርገዉ ግምገማ ይወስናል።

https://p.dw.com/p/36JNr
Karte Äthiopien englisch

(Beri.Mekelle) TDLM´s Plan - MP3-Stereo

  የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምህት በትግሪኛ ምሕፃሩ) ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬ ድርጅታቸዉ አቋም፤ መርሕ እና የወደፊት የትግል ሥልቱን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቁ። ትናንት 2500 የቀድሞ ሽምቅ ተዋጊዎችን አስከትለዉ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት አቶ መኮንን እንደሚሉት ድርጅታቸዉ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ተቀላቅሎ፤ በትብብር ወይም ለብቻዉ መታገል አለመታገሉን በቅርቡ በሚያደርገዉ ግምገማ ይወስናል። ላለፉት አስራ-ሰባት ዓመት የኢትዮጵያን መንግስት በነፍጥ ሲወጋ የነበረዉ ንቅናቄ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰዉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረገዉ ሥምምነት መሠረት ሠላማዊ ትግል ለማድረግ ወስኖ ነዉ።ትናንትና መንገድ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ አራት የንቅናቄዉ የቀድሞ ታጣቂዎች ሞተዋል። 20 ቆስለዋል።

 ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ