1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ምክር ቤት አባላት ጉብኝት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 17 2010

ከልዑካን ቡድኑ መካከል በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታውን የሚያፋጥኑ  ተግባራት እንዲከናወኑ እና ሰብዓዊ መብቶችም እንዲከበሩ ጥሪ የሚያስተላልፈውን ኤች አር 128 የተባለውን ህግ ያረቀቁ እና እንዲጸድቅ ጥረት ያደረጉት ኮንግረስማን  ክሪስ ስሚዝ ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/33dsE
Washington Kongressgebäude bei Nacht
ምስል picture alliance/AP/D. Ake

የአሜሪካን ምክር ቤት አባላት ጉብኝት

 

የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው። እንደራሴዎቹ 5 ናቸው። ከመካከላቸው በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታውን የሚያፋጥኑ  ተግባራት እንዲከናወኑ እና ሰብዓዊ መብቶችም እንዲከበሩ ጥሪ የሚያስተላልፈውን ኤች አር 128 የተባለውን ህግ ያረቀቁ እና እንዲጸድቅ ጥረት ያደረጉት ኮንግረስማን  ክሪስ ስሚዝ ይገኙበታል። የልዑካን ቡድኑ ዓላማ የኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ስቴትስን ጥቅም ያገናዘበ ነው ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። 
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ