1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ መለስ ዓለም መግለጫ

ሐሙስ፣ የካቲት 22 2010

ስለ ዲፕሎማቶቹ ቅሬታ ዶቼቬለ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም አዋጁ የውስጥ ጉዳይ ነው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/2tXH8
Äthiopien Meles Alem Sprecher Außenministerium
ምስል DW/G. Tedla

የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ መግለጫ

ኢትዮጵያ ከሁለት ሳምንት በፊት በደነገገችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ምዕራቡ ዓለም ስጋት እና ቅሪታውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥትም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የውጭ ዲፕሎማቶች አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  ያስፈልጋል ያለበትን ምክንያት አስረድቷል። ስለ ዲፕሎማቶቹ ቅሬታ ዶቼቬለ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም አዋጁ የውስጥ ጉዳይ ነው ብለዋል። አቶ መለስ ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ