1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የወገንተኝነት ጉዞ» ለስደተኞች በፈረንሣይ

ዓርብ፣ ሐምሌ 6 2010

ስደተኞች ወደፈለጉበት ቦታ የመዘዋወር እና ድንበር የማቋረጥ መብታቸው እንዲከበር የሚጠይቅ እና የሚደግፍ ከፈረንሣይ ጣሊያን ድንበር አንስቶ እስከ ለንደን የሚዘልቅ የእግር ጉዞ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/31Q2s
Calais Flüchtlinge Lager
ምስል Reuters/P. Rossignol

ስደተኞችን ለመደገፍ የእግር ጉዞ

ስደተኞች ወደፈለጉበት ቦታ የመዘዋወር እና ድንበር የማቋረጥ መብታቸው እንዲከበር የሚጠይቅ እና የሚደግፍ ከፈረንሣይ ጣሊያን ድንበር አንስቶ እስከ ለንደን የሚዘልቅ የእግር ጉዞ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ይኽ «የአንድነት ጉዞ» በሚል ስያሜ ፈረንሣይ ውስጥ ሰብአዊ ድጋፍ በሚሰጡ ኹለት ማኅበራት አማካኝነት የተዘጋጀውና በርካታ በጎ ፈቃደኛ ዜጎችን ያሳተፈው እና ባላፈው ሚያዚያ ወር በፈረንሣይ እና በጣሊያን ድንበር መካከል በምትገኘው ቬንተሚል ከተማ የተጀመረው የእግር ጉዞ እስካሁን 1400 ኪሎ ሜትሮችን መሸፈኑ ተገልጧል።

በያዝነው ሳምንትም ተጓዦቹ በርካታ ስደተኞች የሚገኙባት እና ወደ እንግሊዝ ለመግባት ሙከራ የሚደረግባት የካሌ ከተማ ደርሰዋል። ካሌ ውስጥም በሰብአዊ ርዳታ ሰጪ ተቋማት እና እዛ በሚገኙ ስደተኞች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። እነዚሁ የእግር ተጓዦች ዓላማቸውን ለማሳካትም ወደ እንግሊዝ በማቅናት ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ጉዟቸውን ቀጥለዋል። ከተጓዦቹ መካከል የተወሰኑት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መኾናቸው ታውቋል። 

ሃይማኖት ጥሩነህ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ