1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወሰን ግጭትን ለመፊታት  የሚቋቋመዉ ኮሚሽን  

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ ሰኔ 11 2010

ባለፈዉ ሳምንት በኢትዮጵዮጵያ ዉስጥ በደቡብ ብሔር፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ብሔር ተኮር ግጭቶች መከሰታቸዉ ተዘግበዋል። በተከሰተዉም ግጭት በተለይም በሃዋሳ፤ በዋላይታ ሶዶና በዋልቂጤ አካባቢዎች የብዙ ሰዉ ሕይወት ጠፍቶአል ንብረትም እንደወደመ ተገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/2znUj
Äthiopien Addis Abeba Premierminister Abiy Ahmed
ምስል Reuters/T. Negeri

የወሰን ግጭትን ለመፊታት  የሚቋቋመዉ ኮሚሽን  

በኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን «የአመራር ለዉጥ» ተከትሎ መንግስት እየሰራ ያለዉን የሰላምና መረጋጋት ስራዎች «ወደ ኋላ ለመመለስ የሚጥሩ ግለሰቦችና ቡድኖች» እንዳሉ ጠ/ሚ ዶኮተር አብይ አሕመድ ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት ቀርበዉ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ገልፀዋል። ሕዝቡ የሚያነሳቸዉ የወሰንና የማንነት ጥያቄ እንዳለ ሆኖ እየታየ ላለዉ ግጭት «ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች» አስተዋጽኦ እንዳለበት ጠ/ሚንስትሩ ባላፈዉ አርብ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ  ግጭት ተሳትፈዋላ ያሏቸዉ ቡድኖችና ግለሰቦች መቀስቀስ የሞከሩት ግጭት በተለያዩ ብሔሮች መካከል ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል መሆኑንም በመግለጫቸዉ ተናግረዋል። በሃገርቱ በተለያዩ ቦታዎች የዞን እንዲሁም የክልል ጥያቄ እንደሚነሳ የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትሩ ለጥያቄ መልስ የሚሰጥ ኮሚሽን እንደሚያቋቁሙ ተናግረዋል።

የሚቋቋመዉ ኮሚሽን በሃገርቱ የሚታየዉን የወሰን ግጭት እውነተኛ መፍትሄ ለመስጠት ከምንም ተጽዕኖ ነፃና ትክክለኛ ስራ መስራት እንዳለበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በብሔርና ማንነት ላይ ጥናት የሚሰሩ አቶ ዳዊት ዮሴፍ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

እንድ አይነት ኮሚሽን ለማቋቋም ግዜ የወሰደበትን ምክንያት ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጀምሮ እስከ 2008 ዓ/ም ድረስ የነበረ ከዛም በኋላ እስካሁን ያለዉን ሁኔታ ማየት እንደምያስፈልግ በወልቂጤ ዩኒቬርስት የፖለትካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት አቶ ዳንኤል መኮንን ይናገራሉ።

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አሕመድ ባለፈዉ ሳምንት ግጭት በታየባቸዉ ቦታዎች ማለትም በሃዋሳ፤ በዋላይታ ሶዶና በወልቅጤ በዚህ ሳምንትም በመጓዝ ከማህበረሰቡ ጋር ለመነጋገር እቅድ እንዳላቸዉ ተናግረዋል። የደቡብ ብሔር፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከ56 በላይ ብሔሮችን አንድ ላይ አቀፎ የያዘ ሲሆን ከ20 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እንዳለበት ይገመታል።

መርጋ ዮናስ 
አዜብ ታደሰ