ራይላ ኦዲንጋ የሚመሩት ጥምረት ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ምርመራ እንዲደረግ ፈቅዷል
ሰኞ፣ ነሐሴ 22 2009ማስታወቂያ
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ኮሚሽኑን የመረጃ ማስቀመጫ ሰንዱቅ እና ለድምፅ ቆጠራ ግልጋሎት ላይ የዋሉ መሳሪያዎች እንዲመለከቱ/እንዲፈትሹ ፈቃድ ሰጥቷል። ውሳኔው የተላለፈው ራይላ ኦዲንጋ የሚመሩት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ነው። በውሳኔው ላይ ማንም አስተያየት መስጠት አይችልም። የምርጫ ኮሚሽኑ ባለሥልጣናት ባለፈው ወር በተካሔደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኬንያታ በ1.4 ሚሊዮን የድምፅ ብልጫ አሸንፈዋል ማለታቸው አይዘነጋም። ውጤቱን አንቀበልም ያሉ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ጠንካራ ይዞታቸውን እንደሆኑ በሚነገርላቸው አካባቢዎች የተበታተነ ተቃውሞ አድርገዋል። ከምርጫ ጋር በተገናኘ ኹከት ቢያንስ 28 ሰዎች ተገድለዋል። አብዛኞቹ የተገደሉት ደግሞ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት እንደሆነ ይነገራል። ለመሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የድኅረ ምርጫ ኹከት ለማያጣት ኬንያ ምን ማለት ይሆን?
ፍቅረ ማርያም መኮንን
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ