1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማረቆ ብሄር ተወላጆች ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2011

በደቡብ ክልል የሚገኙት የማረቆ ብሄር ተወላጆችም ብሄር ተኮር ጥቃቶች እንዲቆሙና በወሰን መከላል የሚነሱ ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ሲሉ ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል፡፡በመስቃን እና በማረቆ ግጭት ከቀያቸው የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች በቤተ-እምነቶች በድንኳን ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ የሰልፉ ተሳፊዎች ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/39xyG
Demonstration der Gemeinde Mareko in Hawassa in Äthiopien
ምስል DW/S. Wegayehu

የማረቆ ብሄር ተወላጆች ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ

ከትውልድ ቀያቸው የጉራጌ ወረዳ ተጉዘው በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ዜጎች ሕግ ባለመከበሩ ምክንያት ለሞት፣ ስደት እና እንግልት መዳረጋቸውን ተናገሩ። በደቡብ ክልል የሚገኙት የማረቆ ብሄር ተወላጆችም ብሄር ተኮር ጥቃቶች እንዲቆሙና በወሰን መከላል የሚነሱ ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ሲሉ ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል፡፡በመስቃን እና በማረቆ ግጭት ከቀያቸው የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች በቤተ-እምነቶች በድንኳን ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ የሰልፉ ተሳፊዎች ተናግረዋል። የሐዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተጨማሪ ዘገባ አለው። 
ሸዋንግዛው ወጋየሁ 
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ