«ምርጫ ቦርድ ፓርቲያችንን አፍርሶብናል»ኢዴፓ
ሰኞ፣ ሐምሌ 30 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በህምጻሩ ኢዴፓ አመራር አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲያችንን አፍርሶብናል ሲሉ አስታወቁ። የአመራር አባላቱ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ በምርጫ ቦርድ ድርጊት ምክንያት ህልውናችንን አጥተናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ ኤዴፓ አልፈረሰም ሲል አስታውቋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የኤዴፓን መግለጫ ተከታትሏል፤ የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊንም አነጋግሯል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ