የኢትዮ-ቤልጂግ እግር ኳስ ቡድን
ረቡዕ፣ ነሐሴ 2 2010ማስታወቂያ
የዘንድሮዉ የኢትዮጵያዉያን አዉሮጳዉያን የስፖርት እና የባሕል ድግስ ባለፈዉ ሳምንት ሽቱትጋርት ደቡብ ምዕራብ ጀርመን ዉስጥ ተደርጓል። እስካለፈዉ ዕሁድ ድረስ ለአራት ቀን የተካሄደዉ ድግሥት የዝግጅት መሳከር፤ መዝረክረክ እና መተራመስ የተፈጠረበት እንደነበር የበዓሉ ተሳታፊዎች እየተቹ ነዉ። ይሁንና ዘንድሮም እንደከዚሕ ቀደሙ ሁሉ በተለያዩ ሐገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የተደራጁ የእግር ኳስ ቡድናት ያደረጉት ግጥሚያ የድግሱ ዋነኛ አካል ነበር። በግጥሚያዉ ከተካፋሉት ቡድናት አንዱ የነበረዉን የኢትዮ-ቤልጂግን የእግር ኳስ ታሪክ የብራስልሱ ወኪላችን ዳግማዊ ሲሳይ ያወጋናል።
ዳግማዊ ሲሳይ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ