1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ እና መፍትሔው

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 24 2010

የኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎችን በአንዴ ያዳረሰው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከተጀመረ እነሆ ሁለት ዓመት ሆነው፡፡ “ለመሆኑ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ምንድነው?” ሲል የዶቼ ቬለዉ ያን ፊሊፕ ቬልሄልም በዘገባው ይጠይቃል፡፡ “መነሻ ምክንያቶቹ በርካታ እና የተወሳሰቡ ናቸው” ሲልም ጋዜጠኛው ምላሹን ይሰጣል፡፡

https://p.dw.com/p/2qFUb
Äthiopien Tote bei Anti-Regierungs-Protesten in Bishoftu
ምስል DW/Y. Gegziabher

የቀውሱ መነሻዎች “በርካታ እና ውስብስብ” ናቸው

ለጋዜጠኛው ለማርቲን ፕላውት ነገሩ ግልጽ ነው፡፡ እርሱ እንዳለው አሁን በኢትዮጵያ የሚታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ የችግሩቹ ሁሉ መነሻ ተቋጥረው የተቀመጡበት ነው፡፡ “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት እና አቶ መለስ ዜናዊ የዲሞክራሲ ስርዓት እና እውነተኛ ፌደራሊዝምን በሀገሪቱ በኢትዮጵያ ለመዘርጋት ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ አላማቸውም አይደለም፡፡ በህገመንግስቱ አንቀጽም ላይ እንደሚታየው እነሱ ያተኮሩት በብሔር ልዩነት እና በብሔር ክፍፍሉ ላይ ነበር፡፡ በብሔር ልዩነት ላይ አተኩሮ አንድ ሀገር እና አንድ መንግስት ለመመስረት የሚጥር ኃይል ደግሞ በመጨረሻ እርሱ የሚያጭደው የብሔር ጥላቻ እና በብሔር ላይ የተመሰረተ ግጭቶችን ነው ” ብለዋል ፕላውት፡፡

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጉዳዮችን በቅርበት የሚከታተሉት ጋዜጠኛ ማርቲን ፕላውት “የሆነው ይሁን ኢትዮጵያ ተፈረካክሳ እና ተበታትና ከዓለም ካርታ ላይ አትጠፋም” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ እንደጋዜጠኛው ሁሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም “ኢትዮጵያ በምንም ዓይነት ተፈረካክሳ አትወድቅም” ባይ ናቸው፡፡ የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል ያጠናቀረውን ሙሉ ዘገባ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ፡፡   

 ያን ፊሊፕ ቬልሄል/ ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ