1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እርቀ ሰላም

ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2010

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሀገር ውጭ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር ለሚደረገው ዕርቀ ሰላም ሦስት ሊቃነ ጳጳሳትን እንደምትልክ ተገለፀ። ትናንት አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ዕርቀ ሰላሙን አክሎ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ ተነጋግሯል።

https://p.dw.com/p/31Hqu
Äthiopien Marienkirche Hl Maria von Zion in Aksum
ምስል Imago/Chromorange

ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ወደ አሜሪካ ይላካሉ

በዚሁ መሠረትም ለዕርቀ ሰላሙ የሚላኩት የሃይማኖት አባቶች የሚደርሱበትን ውሳኔ እንደሚቀበል ነው የተገለጸው። በቤተ ክርስቲያኒቱ ከሁለት ዓስርት ዓመታት በላይ የጠፋውን ሰላም ለመመለስ ከ2003ዓ,ም ጀምሮ ጥረት ሲደረግ መቆየቱም ተመልክቷል። የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ሂደት እንዲሳካም ገዳማት እና አድባራት እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን  በጸሎት እንዲተጉም ጥሪ ቀርቧል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ