የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አዲስ አካሄድ
እሑድ፣ መስከረም 27 2011ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ብሄራዊ ምርጫ በተለያዬ ሂደትና ሁኔታ ሲደረግ የቆዬ ቢሆንም፤ ሀገሪቱ በቀጣይ ልታካሂደዉ ያሰበችዉ ምርጫ ግን ብዙወችን እያነጋገረ ነዉ። ምክንያቱ ደግሞ ሀገሪቱ በጀመረችዉ አዲስ የለዉጥ ጎዳና ሀገር ቤት ከሚገኙት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተጨማሪ በትጥቅ ትግል ሳይቀር ይታገሉ የነበሩ ድርጅቶች ከዉጭ ወደ ሀገር ቤት በገቡበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ነዉ። ለመሆኑ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከዉጭ የመጡትን ፓርቲዎች ከሀገር በቀሎቹ ጋር አብሮ ለማስተናገድ ምን ዝግጅት እያደረገ ነዉ። ባልደረባችን ጌታቸው ተድላ ሀይለጊዮርጊስ የቦርዱን የህዝብ ግንኙነት አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ጌታቸው ተድላ ሀይለጊዮርጊስ
ጸሀይ ጫኔ
አዜብ ታደሰ