1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስምምነቱ «ጠቃሚ ነዉ» ሼሕ መሐመድ አሚን ጀማል

ረቡዕ፣ ሰኔ 27 2010

ቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ትናንት በጠሩት ስብሰባ ላይ የተካፈሉት የሁለቱ ወገኖች መሪዎች እንደሚሉት ሙስሊሙን ሕብረተሰብ ከሚከፋፍሉ እርምጃዎች ታቅበዉ ለጋራ ዓላማ ተባብረዉ ይሰራሉ።የጠቅላይ ምክር ቤቱ እና የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች ትናንት የጋራ ኮሚቴ መሥርተዋል።ይቅር ተባብለዋልም

https://p.dw.com/p/30qHY
Screenshot Facebook Äthiopien
ምስል Facebook/Office of the Prime Minister-Ethiopia

MMT (Interview)Ethiopian muslim Council President Mohammed Amin Jemal - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የሙስሊሙን ጥያቄ ለመፍታት በጋራ እንደሚጥሩ አስታወቁ።ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ትናንት በጠሩት ስብሰባ ላይ የተካፈሉት የሁለቱ ወገኖች መሪዎች እንደሚሉት ሙስሊሙን ሕብረተሰብ ከሚከፋፍሉ እርምጃዎች ታቅበዉ ለጋራ ዓላማ ተባብረዉ ይሰራሉ።የጠቅላይ ምክር ቤቱ እና የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች ትናንት የጋራ ኮሚቴ መሥርተዋል።ይቅር ተባብለዋልም።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼሕ መሐመድ አሚን ጀማል እንዳስታወቁት ትናንት የተደረገዉ ዉይይት እና ስምምነት የሙስሊሙን ሕብረተሰብ አንድነት እና ጥቅም ለማስጠበቅ ጠቃሚ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ሼሕ መሐመድ አሚን ጀማልን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ