«ስምነቱ ተስፋ ሰጪ ነዉ»አሕመዲን ጀበል
ረቡዕ፣ ሰኔ 27 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባለሥልጣናት እና የሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች ትናንት የደረሱበትን ሥምምነት እና የወደፊት ዕቅዳቸዉን ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ለሙስሊሙ ሕብረተሰብ ይፋ አድርገዋል።የትናንቱ ዉይይት እና ሥምምነት እስካሁን የነበረዉን የሙስሊሙን ማሕበረሰብ ጥያቄ ለመመለስ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አዲስ የተዋቀረዉ ኮሚቴ እና የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴም አባል ደራሲ አሕመዲን ጀበል አስታዉቀዋል።አቶ አሕመዲን እንደሚሉት መንግሥት ከእንግዲሕ በሙስሊሞች ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ቃል ገብተዋል።ደራሲ አሕመዲን ጀበልን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ