1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያንን የጋራ መርሃ ግብር

ሰኞ፣ ነሐሴ 28 2010

ቤልጂግ የሚኖሩ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ተወላጆች ተወላጆች ባለፈው ቅዳሙ በኮርትሬክት ከተማ ባዘጋጁት የጋራ መርሃ ግብር ላይ የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ይበልጥ እንዲጎለብት እና አንድ በሆኑት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች መካከል የተፈጠረው ግንኙነት ይበልጥ እንዲዲሰፋ በማሳሰብ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/34EWT
Anhänger von Eritrea und Äthiopien
ምስል Chuleye Mesaye

የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያን መርሃ ግብር በቤልጂግ

 

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት በመካከላቸው የነበረውን አለመግባባት እና ወደ ጦርነት ሊያመራ የሚችለውን ፍጥጫ በማስወገድ ሰላም ለማውረድ በመቻላቸው በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን እና ኤርትራውያን  በልዩ ልዩ የጋራ መርሀ ግብሮች ደስታቸውን እየገለጹ ነው። ቤልጂግ የሚኖሩ የሁለቱ ሀገራት ተወላጆችም ባለፈው ቅዳሙ በኮርትሬክት ከተማ ባዘጋጁት የጋራ መርሃ ግብር ላይ የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ይበልጥ እንዲጎለብት እና አንድ በሆኑት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች መካከል የተፈጠረው ግንኙነት ይበልጥ እንዲዲሰፋ በማሳሰብ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ገበያው ንጉሴ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ