1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉያን የለዉጥ ድጋፍ ስብሰባ በቤልጂየም

ሰኞ፣ ሐምሌ 23 2010

በኢትዮጵያ ይፈፀሙ የነበሩትን የሰብዓዊ መብቶችንና አምባገነናዊ  አስተዳደር በመቃወም በአዉሮጳ ከተሞችና አደባባዮች ይተሙ የነበሩ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ አመራር የተጀመረዉ የለዉጥ አመራር እንዲቀጥልና ግቡን  እዲመታ በአደባባይና በልዩ ልዩ ዘዴዎች እየገለፁ ነዉ።

https://p.dw.com/p/32KNG
Google Hangout ANDERES FORMAT EU Europa Brüssel
ምስል imago/imagebroker

በኢትዮጵያ ይፈፀሙ የነበሩትን የሰብዓዊ መብቶችንና አምባገነናዊ  አስተዳደር በመቃወም በአዉሮጳ ከተሞችና አደባባዮች ይተሙ የነበሩ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ አስተዳደር የተጀመረዉ የለዉጥ አመራር እንዲቀጥልና ግቡን እዲመታ በአደባባይና በልዩ ልዩ ዘዴዎች እየገለፁ ነዉ። የኢትዮጵያዉያን የብሶት መግለጫና የተቃዉሞ ማስተጋብያ የነበረችዉ ብራስልስም የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድን የመደመር ጽንሰ ሃሳብና የለዉጥ መርሃግብር የሚያቀነቅኑ ኢትዮጵያዉያን  የሚሰባሰቡባት እና የተጀመረዉ የለዉጥ ሂደት መዳረሻ፤ ዲሞክራሲያዊ ግቡም ሠላምና ብልፅግና እንዲሆን የሚመክሩባት ሆናለች። በዚህም መሠረት ባለፈዉ ቅዳሜ በቤልጂየም እና በአካባቢዉ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የተሳተፉበት የኢትዮጵያ የለዉጥ ሂደትና ተግዳሮቶቹ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሕዝባዊ ዉይይት ተካሂዷል። ስብሰባዉን ያዘጋጀዉ ድልድይ በአዉሮጳ የኢትዮጵያዉያን መድረክ የተሰኘ ስብስብ ሲሆን፤ ለመጀመርያ ጊዜም በቤልጂየም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጋበዘበትና አምባሳደሩ አቶ እዉነቱ ብላታ ደበላ በዋና ተናጋሪነት የተሳተፉበት ነበር። በዚሁ ስብሰባ ላይ ነባሩ ፖለቲከኛ አቶ አበራ የማነ አብና እና የሰብዓዊ መብት አቀንቃኙ አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያምም ተገኝተዉ ነበር።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ