የኢሬቻ በዓል
ዓርብ፣ መስከረም 19 2010ማስታወቂያ
ቢሾፍቱ የኢሬቻን በዓል የፊታችን እሁድ ለማከበር እየተዘጋጀት ነው። በአምናው የቢሾፍቱ ሆራ በዓል ላይ የሰዎች ህይወት መጥፋቱ እና በርካቶችም መጎዳታቸው በዘንድሮው በዓል ላይ ጥላ ቢያጠላበትም በዓሉን እንደ ልምድ እና ወጉ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን በዚያ የሚገኘው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ገልጾልናል። በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ፖሊስ እንደማይገኝ ሆኖም ከዛ ውጭ በፍተሻ እንደሚሳተፍ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ዮሐንስን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ