1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢህአዴግ ውሳኔ እና የሂውመን ራይትስ አስተያየት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 26 2010

የኢትዮጵያ መንግሥት የተፈረደባቸው ወይም ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉየፖለቲካ አመራሮችን እንደሚፈታ ያስታወቀበት ድርጊት ወሳኝ ርምጃ መሆኑን የመብት ተሟጋቹ ድርጅት፣ ሂውመን ራይትስ ዎች አስታወቀ። ሆኖም፣ ውሳኔው ብዙ መሻሻሎች ሊደረጉበት የሚገባ ነው ሲል አሳስቧል።

https://p.dw.com/p/2qLRZ
Human Rights Watch Logo Flash-Galerie
ምስል Human Rights Watch

ውሳኔው ተስፋ ሰጪ ነው።

ሂውመን ራይትስ ዎች ይህን ያለው ትናንት አራቱ የገዢው የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ ኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች መሪዎች በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንደሚፈቱ እና የማዕከላዊ  የምርመራ እስር ቤትም እንደሚዘጋ ያስታውቁበትን ውሳኔ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ነው።

አክመል ነጋሽ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ