1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፋር እና የኢሳ ህብረተሰብ ውዝግብ

ሐሙስ፣ ጥር 9 2011

የሶማሌና አፋር ክልላዊ መስተዳድሮች ወሰን ላይ የሚገኘው ህብረተሰብ ለዘመናት ከግጦሽ መሬትና ከውሀ ጋር የሚጋጥሙትን ችግሮች ባለው ባህል ሲፈታ ነው የኖረው። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ገዳማይቱ ፣አደይቱ እና እንዱፎ በተባሉ የድንበር አካባቢ ቀበሌዎች ባነሱት የግዛት ይገባኛል ጥያቄ ንትርክ የሰው ህይወትና ንብረት ያጠፋ ንትርክ ውስ ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/3Bjnj
Äthiopien - Heißester Ort der Erde
ምስል DW/J. Martinez

የአፋር እና የኢሳ ህብረተሰብ ውዝግብ

የፌደራል መንግስት ጭምር የተሳተፈበት የሶስቱ ቀበሌዎች ይገባኛል ጥያቄ ስምምነት ነጥብ አለመከበር ከሰሞኑ ብቻ ግጭት በማስከተል አገር አቋራጭና ድንበር ተሻጋሪ መንገዶች ጭምር እንዲዘጉ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ እንዲፈጠር አድርጓል ፡፡ ትናትም ከዚሁ ከተጎራባች ክልሎቹ የወሰን ችግር ጋር በተያያዘ የአፋር ክልል ልዩ ሀይል ከህብረተሰቡ ጋር ባለመግባባት ወሰደው የተባለውን የሀይል ጥቃት ተከትሎ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ፣ መጎዳታቸውንና ከአካባቢ መፈናቀላቸውን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አደም ፋራህ ገልፀው በአሁኑ ወቅት ለተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍና እርዳታ እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡ አቶ አደም ለDW እንደገለፁትበአፋር ክልል  ልዩ ሀይል የደረሰውን ይህን ጥቃት ተከትሎ በክልሉ የሲቲ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች ተቃውሞ ሰልፍ ከማካሄድ በተጨማሪ ከድሬደዋ ቡቲ የሚወስደው ዋና መንገድ እንዲዘጋ ያደረገ ቢሆንም ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት ከትናንት ለሊት ጀምሮ መንገዱ እንዲከፈት ተደርጓል ፡፡ በአካባቢው የሚገኘው ሕብረተሰብ ከሚያነሳቸው ጥቄዎች በተጨማሪ በአካባቢው ሰላም መፈጠር ለራስ ጥቅም አይበጅም በሚል ሰላም እንዳይፈጠር የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን የገለፁት አቶ አደም ከነዚህም አመራሩ ፣ ኮንትሮባዲስቶችና ሌሎች ፀረ ሰላም ሀይሎች የሚገኙ መሆናቸውንና  በነዚህ አካላት ላይ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ለዘላቂ ሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡ከዚህ ጎን ለጎን የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተቀናጅቶ ለመፍታት ስምምነት መደረሱን ተናግረዋል ፡፡ ከትናንት ጀምሮ ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የድሬደዋ ጅቡቲ መንገድ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ መጀመራቸውን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡ ፡ 

መሳይ ተክሉ

አርያም ተክሌ

ተስፋለም ወልደየስ