1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ቤተ-መንግሥት ዉጥረት

ረቡዕ፣ መስከረም 30 2011

ዉጥረቱ ማምሻዉ ላይ ረግቧል። መንገዶችም ተመልሰዉ ተከፍተዋል። ይሁንና በቅጡ የታጠቁ ወታደሮችን የጫኑ የጦር ተሽከርካሪዎች እና ቃኚ ወይም ፓትሮል የሚባሉት አነስተኛ የጦር ሠራዊት መኪኖች ቤተ-መንግሥቱ አካባቢ ሲመላለሱ ነበር።

https://p.dw.com/p/36JPH
Addis Abeba
ምስል Haile

MMT (Q&A) Tension in and around National Palace in AA - MP3-Stereo

አዲስ አበባ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት አካባባቢ ዛሬ ዉጥረት ፤ ግርግር እና መሳከር ሰፍኖ፤ ወታደራዊ ንቅናቄ ሲደረግ መዋሉን የአይን ምስክሮች አስታወቁ። ብሔራዊ  (ኢዮቤልዩ)-ቤተ መንግስትን ታከዉ የሚያልፉ መንገዶች ተዘገዉተም ነበር። መላዉ አዲስ አበባም ከማርፈጃዉ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ ነዉ የዋለዉ። አካባቢዉን የቃኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደሚለዉ ዉጥረቱ ማምሻዉ ላይ ረግቧል። ሆኖም ማምሻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተለያዩ ግዳጆች ላይ የቆዩ የሠራዊቱ አባላት ጋር ተገናኝተው ስለሚያሳስቧቸው ጉዳዮች መወያየታቸውን በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

ዩሐንስን ገብረእግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ