1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር ንብረት ለውጥ እና ጣጣው

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 6 2011

በቅርቡ ኢንዶኔዥያን የመታው አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ጎርፍ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ሲያሳጣ በንብረት ላይም ያደረሰው ውድመት ቀላል የሚባል አይደለም።  በአውሮጳም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ የመጣው የአየር ሁኔታ የአየር ንብረት ለውጥ ውጤት መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/36eAR
Usbekistan Aralsee Symbolbild Klimawandel Dürre
ምስል picture-alliance/blickwinkel/G. Pohl

የከፋ የአየር ጠባይ ልውውጥ የሚያስከትለው የአየር ንብረት ለውጥ

 ከዓመታት በፊት በዚህን ወቅት በአውሮጳ ከባድ ቅዝቃዜ የነበረ ሲሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት እየታየ የመጣው የመሞቅ አዝማሚያ ሀገራቱን ማሳሰቡም አልቀረም። እንደ ዘርፉ ምሁራን አነጋገር ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂው ያደጉት ሃገራት ወደ ከባቢ አየር የሚለቁት የካርቦንዳይ ኦክሳይድ መጠን መጨመር ነው። የኪዮቶውና የፓሪስ ስምምነቶች እነዚሁ ሃገራት ዓለምን ከባሰ ጥፋት እንዲታደጉ በአስገዳጅነት የገቡት ውል ቢሆንም ለማክበር ማንገራገር አንዳንዴም ጥሎ መውጣትም እየታየበት ነው። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።

ዳግማዊ ሲሳይ

ሸዋዬ ለገሠ