1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እርዳታው ለጋራ ጸረ ሽብር ኃይል ማጠናከሪያ ይውላል

ሐሙስ፣ ሰኔ 1 2009

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ወይዘሮ ፌዴሪካ ሞጎህሮኒ ባለፈው ማክሰኞ በማሊ መዲና ባማኮ ከአምስቱ የሳህል ቡድን አባል ሃገራት ጋር ስብሰባ ካደረጉ በኋላ እርዳታውን ይፋ አድርገዋል፡፡

https://p.dw.com/p/2eMH5
Mali Soldaten ARCHIV
ምስል dapd

Ber. Brussles (EU to give 50 million Euros for African force in Sahel) - MP3-Stereo

የአውሮጳ ኅብረት በምዕራብ አፍሪካ በተለይ በሳህል አካባቢ በሚገኙ አገሮች ለተቋቋመው የጋራ ጸረ ሽብር ኃይል ማጠናከሪያ 50 ሚሊዮን ዮሮ የለገሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡ እርዳታውን ይፋ ያደረጉት ከትላንት ወዲያ ማክሰኞ በማሊ መዲና ባማኮ ከአምስቱ የሳህል ቡድን አባል ሃገራት ጋር ስብሰባ ተቀምጠው የነበሩት የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ወይዘሮ ፌዴሪካ ሞጎህሮኒ ናቸው፡፡ እንደ ጎርጎሮሳዊው 2014 የተመሠረተው የሃገራቱ ቡድን ቦርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ ሞሪታንያ፣ ኒጀር እና ቻድን ያቅፋል፡፡ ዓላማው ደግሞ የየሃገራቱን የአስተዳደር እና የጸጥታ ሁኔታ በማጠናከር አካባቢውን ከሽብርተኞችና ከሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በመከላከል የተረጋጋ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሆነ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የአውሮጳ ኅብረት መቀመጫ በሆነችው ብራስልስ የሚገኘው ዘጋቢያችን ኅብረቱ ለመርሃ ግብሩ ማስፈጸሚያ ስለለገሰው እርዳታ ዘገባ ልኮልናል፡፡ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ መስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡

 

ገበያው ንጉሤ

ተስፋለም ወልደየስ

ሸዋዬ ለገሠ