1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኞች ዕጣ

ዓርብ፣ ሰኔ 22 2010

መሪዎቹ ስደተኞቹ ይሰፍሩበታል ተብለዉ የሚታሰቡ የአፍሪቃ ሐገራትም ሆነ የስደተኞቹን  ፍላጎት ከቁብ የቆጠሩት አይመስሉም።በስምነቱ መሠረት ስደተኞቹ አፍሪቃ ዉስጥ ከሠፈሩ በኋላ ከመሐላቸዉ እየተመረጡ  ወይም አሳማኝ ምክንያት አላቸዉ የሚባሉት ወደ አዉሮጳ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።

https://p.dw.com/p/30ZEL
Symbolbild EU Flaggen
ምስል AFP/Getty Images/Y. Herman

(Q&A) EU-Summit - MP3-Stereo

የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች በሥደተኞች አቀባበል ሰበብ የገጠሙትን ዉዝግብ አስወገዱ።መሪዎች ዛሬ የሁለት ቀን ጉባኤያቸዉን ሲያጠቃልሉ ወደ አዉሮጳ ለመግባት የሚፈልጉ ስደተኞች አፍሪቃ ዉስጥ እንዲሰፍሩ ወስነዋል።የሚሰፍሩበትን የአፍሪቃ ሐገር ወይም ሐገራት ሕብረቱ እንዲያፈላልግ ሐላፊነት ሰጥዉታል።መሪዎቹ ስደተኞቹ ይሰፍሩበታል ተብለዉ የሚታሰቡ የአፍሪቃ ሐገራትም ሆነ የስደተኞቹን  ፍላጎት ከቁብ የቆጠሩት አይመስሉም።በስምነቱ መሠረት ስደተኞቹ አፍሪቃ ዉስጥ ከሠፈሩ በኋላ ከመሐላቸዉ እየተመረጡ  ወይም አሳማኝ ምክንያት አላቸዉ የሚባሉት ወደ አዉሮጳ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ