1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቡነ ማቲያስ የአዲስ ዓመት መግለጫ 

ዓርብ፣ ጳጉሜን 2 2010

አቡነ ማትያስ ዛሬ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ህዝቡ ከምንም በላይ ለፍቅር እና ቦታ እንዲሰጥ ተማጽነዋል። በሀገሪቱ የሚካሄደው ለውጥ እንዳይሰናል ህብረተሰቡ በመጪው ዓመት መቃቃር እና ጥላቻን ከሚያስከትሉ አባባሎችም እንዲርቅም ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/34Vcb
Äthiopien Synode | Patriarch Matias
ምስል DW/Getachew Tedla

የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫ 

ለኢትዮጵያ አንድነት የሚበጀው እግዚአብሔርን እና ህዝቡን ማዕከል አድርጎ መሥራት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ተናገሩ ። አቡነ ማትያስ ዛሬ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ህዝቡ ከምንም በላይ ለፍቅር እና ለአንድነት ቦታ እንዲሰጥ ተማጽነዋል። በሀገሪቱ የሚካሄደው ለውጥ እንዳይሰናል ህብረተሰቡ በመጪው ዓመት መቃቃር እና ጥላቻን ከሚያስከትሉ አባባሎችም እንዲርቅም ጠይቀዋል። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።  
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ