1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርቲስት ፈቃዱ ተክለ ማርያም ቀብር

ሐሙስ፣ ሐምሌ 26 2010

የአርቲስት ፈቃዱ ተክለ ማርያም የቀብር ስነ ስርዓት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ዛሬ በአዲስ አበባ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

https://p.dw.com/p/32XRy
Äthiopien Beerdigung des Künstlers Fekadu in Addis Abeba
ምስል DW/Getachew Tedla

የአርቲስት ፈቃዱ ቀብር

 

የታዋቂው እና የተወዳጁ አርቲስት ፈቃዱ ተክለ ማርያም የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በአዲስ አበባ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። በቀብሩ ስነ ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል። በበርካታ የመድረክ ቲያትሮች፣ በራድዮ እና በቴሌቪዥን ድራማዎች እንዲሁም ፊልሞች ላይ በመተወን እውቅናን ያተረፈው ፈቃዱ በመጽሐፍት ትረካውም ይደነቃል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የቀብር ስነ ስርዓቱን ተከታትሏል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ