1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል አመራር በአሜሪካ

ረቡዕ፣ ኅዳር 26 2011

ባለፈው እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው ውይይት ላይ የአማራ ክልል ተወላጆች በትምህርት በጤና በምህንድስና በኢንቬስትመንት እና በሌሎችም መስኮች ሀገራቸውን እንዲረዱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ውይይቱ በሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞችም ይቀጥላል።

https://p.dw.com/p/39XBv
Washington Kongressgebäude bei Nacht
ምስል Getty Images/T. Katopodis

የአማራ ክልል አመራር የአሜሪካ ጉብኝት

በአማራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ የልዑካን ቡድን ዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ የአማራ ተወላጆች እና ደጋፊዎቻቸው ጋር ካለፈው እሁድ ጀምሮ ውይይት እያካሄደ ነው። ባለፈው እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው ውይይት ላይ የአማራ ክልል ተወላጆች በትምህርት በጤና በምህንድስና በኢንቬስትመንት እና በሌሎችም መስኮች ሀገራቸውን እንዲረዱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ውይይቱ በሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞችም ይቀጥላል። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን ውይይቱን የተከታተሉ የዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎችንም አስተያየት ያካተተ ዘገባ   ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ