1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔልሰን ማንዴላ 100 ዓመት

Merga Yonas Bula
ዓርብ፣ ሐምሌ 6 2010

ኔልሰን ማንዴላ በህይወት ቢኖሩ የፊታችን ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም 100 ዓመት ይሞላቸው ነበር። እሳቸዉ የደቡብ አፍሪቃን የዘር መድልኦ ስርዓት አፓርታይድን ታግለው በማስቆም በሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ጥቁር ፕሬዝዳንት ለመሆን በቅተዋል። ማንዴላ ዛሬም ቢሆን ለወጣት አፍሪቃውያን ተምሳሌት ናቸው።

https://p.dw.com/p/31QJH
Madiba House Museum
ምስል DW

የኔልሰን ማንዴላ 100 ዓመት፣ ለወጣት አፍሪቃዉያን አርዓያ

«ስለ ማንዴላ ማውራት ማለት ስለ ትግል መነጋገር ማለት ነዉ። ያም ማለት ለጭቆና እና ፍራሃት አለመንበርከክ ማለት ነዉ።» ይህን ያለው ሞዛምቢካዊዉ የ22 ዓመቱ ዘፋኝ፤ ተማሪና የሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ አንድሬ ካርዶሶ ነዉ። ኔልሰን ማንዴላ አሁን ለእነሱ ምን ማለት እንደሆነ ከተናገሩት በአፍሪቃ ከሚገኙ ከ15ቱ የዶይቼ ቬሌ ወክሎች ዉስጥ አንድሬ ካርዶሶ አንዱ ነዉ።

እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ሐምሌ 1918 የኔልሰን ማንዴላ አባት «ጋድላ» ልጁን ማንዴላን «ሮልሃላሃላ» ብሎ ሲሰይም ምናልባትም ለውጥ የማምጣት አቅሙን ቀደም ብሎ ታይቷቸውም ሳይሆን አይቀርም ። በጦሳ ሕዝብ ቋንቋ «ሮልሃላሃላ» ማለት «ቅርንጫፎችን የሚሰብር» ወይም «ሌላ ሰዉን የሚያናድድ» ማለት ነዉ። ደቡብ አፍሪቃውያን ማዲባ እያሉ በጎሳ ስማቸው የሚጠሯቸው ማንዴላ እውነትም እንደተባለው ህገ ወጥ በሚባለው በደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ላይ ብዙ ችግር ፈጥረውበታል።

Nelson Mandela als junger Anwalt
ምስል AP

በዛን ግዜ በ20ኛዎቹ አጋማሽ እድሜ የነበረዉ ኔልሶን ማንዴላ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1944 ዓ.ም የአፍሪቃን ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤ/ኤን/ሲ) ተቀላቀለ። ከ4 ዓመት በኋላ ደቡብ አፍሪቃን ለማስተዳደር ስልጣን የያዘዉ የዘር መድልዎን ተቋማዊ ያደረገው የነጮቹ «ብሔራዊ ፓርቲ» ሥልጣን ያዘ። የዘር ክፍፍሉም የጅምላ ተቃውሞዎች እና የሲቪል አለመታዘዝ ዘመቻዎችን ቀሰቀሰ። በዝህ ዉስጥም ማንዴላ ዋነኛ ሚና ተጫዉተዋል። በ1961 ኤ/ኤን/ሲ ከታገደ በኋላ ማንዴላ «ኡምኮሆንቶ ዌ ስዚዌ» ወይም «የሕዝብ ጦር» የተባለውን ኃይል አቋቋመ። እንደ ጦር አዛዥ በመንግስት ተቋማት ላይ የሽምቅ ውጊያ እንዲካሄድ መርተዋል።

እ.ኤ.አ. በ1962 የገንዘብ ርዳታን ለማግኘትና ለኤ/ኤን/ሲ ካድሬዎችን ወታደራዊ ስልጠ ለማዘጋጀት በምስጢር ወደ ውጭ አገር ሄደ። ከተመለሰ በኋላም ታሰረ። በእሱ ላይ የተመሰረቱት ክሶች ለሞት ፍርድ የሚያበቃዉ ነበር። ማንዴላ ብዙ ተከሳሾች እንዳደረጉት ሁሉ ማንዴላም ከአገር ለመጥፋት ሞክሮ ነበር። ግን በመጨረሻ ላይ ለመቆየት ወሰነ። አቋሙን ለማሳወቅ ባደረገው ታሪካዊ ንግግር በመጨረሻ ላይ እንደ  ትልቅ ኑዛዜ ሆኖ ተወስደዋል፣ «የነጭም ሆነ የጥቁር የበላይነት እንዲያበቃ ታግያለዉ። ሁሉም ሰዎች እርስ በርስ በመስማማት እና እኩል እድል አግኝቶ የሚኖሩበትን ዲሞክራሲያዊ እና ነፃ የሆነ ኅብረተሰብ እንድኖር የሚለዉን ሃሳብ ተሟግቻለዉ። ለመኖርም ሆነ ለማሳካት ተሰፋ የማድርግበት ሃሳብ ነዉ። ግን፤ ጌታ ከረዳኝ፣ አስፈላጊም  ከሆነ፤ ለመሞት ዝግጁ የሆንኩበት ሃሳብ ነዉ።»

የ30 ዓመቱ የዚምባቡዌ ጋዝጤኛ ምሎንዶሎዚ ንዶሎቩ ኔልሰን ማንዴላ ለጥቁሮቹ ብቻ ሳይሆን እንደ ደቡብ አፍርቃ ፕሬስዳንት በነጮች ላይ የምደረገዉ የትኛዉም የዘር መድሎ ስያወግዝ እንደነበረ ይናገራል፣ «እሱ የመርህ ሰው ነበር፤ በቃላቶች አቋም የምፀና ሰው ነበር። ለኔ ኔልሰን ማንዴላ ማለት የትግል ተምሳሌት ማለት ነዉ።»

ማንዴላ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርደበት። ከኬፕ ታዎን 4 ክሎሜትር ላይ የምትገኝ የሮቢን ደሴት ላይ ለ17 ዓመታት ታሰሩ። አሱ የታሰረዉ የእሥር ቤት ክፍል ቁጥር አምስት ዘሬ የቱሪስት መስህብ ሆኗል። ከ 1988 ጀምሮ ማንዴላ ከእስር ለመፈታት ዝግጅት ማድረግ ጀመረ። ከሦስት ዓመት ቀደም ብሎ ኤ/ኤን/ሲ አመፅ መፍጠር ካቆመ ትለቀቃለህ ተብሎ የቀረበለትን የይቅርታ ጥያቄ ማንዴላ ውድቅ አድርጎታል።

የደቡብ አፍሪቃዉ የነጻነት ተምሳሌት ማንዴላ ከሶስት አሥርተ ዓመታት እስር በኋላ በጎርጎሮሳዊው ፌብሩዋሪ 11 ቀን 1990 በነፃ ተለቀቀ። እንደማንኛውም ጊዜ ለዉጥን የማምጣት ፍላጎቱ ከትልቅ ትሕትናዉ ጋር ተጣመረ። የመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ንግግሩም በድጋሚ የኑዛዜ ቃላቶች ነበሩት፤ «እንደ ነብይ ሳይሆን፤ እንደ ህዝብ ትሁት አገልጋይ እዝ ከፊት ለፊታችሁ ቆምያለዉ። የናንተን ድካምና የከፈላችሁትን የጀግና መስዋዕትነት እኔ እዚህ እንደርስ አብቅቶኛል።። ስለዝህ ቀሪውን ዘመኔን በናንተ ላይ ጥያለዉ።»
ይህ አስተሳሰብ ጋምብያዊዉን የጋዜጠኝነት ተማሪ አነቃቅቷል፤ «እንደ ግለሰብ እኔ የማምነዉ እንደዚህ ያለ ከራስ ወዳድነት ያለፈ አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባል። ለሌሎች ሰዎች ራስን መስዋእት ማድረግ፤ ነገሮች መስፈፀም ያስፈለግላል። ሁሌም ራስ ወዳድ አለመሆን እና እኔ ብቻ ነው ማለት ማቆም። እንደገና፣ የሌሎች ሰዎች ሕይወት እንዲሻሻልና ፊታቸው በፈገግታ እንዲሞላ ምን እያደረገን ነው?»

Nelson Mandela Wahlen 1994
ምስል Walter Dhladhla/AFP/Getty Images

ማንዴላ የዘር ልዩነትን ለማስወገድ የሚያደርገዉን ትግል ቀጥለ። በጎርጎሮሳዊው ሚያዚያ 1994 ደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያ ነጻ ምርጫዋን አከናወነች። በግንቦት 10፤  ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ። ማንዴላ ወደ ስልጣን በህብረተሰቡ መካከል እርቅ ለመፍጠር ትኩረት አደረጉ። ከሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ሞንድ ቱቱ ጋር በመሆንም በአፓርታይድ ጊዜ የተፈጠሩ ወንጀሎችን የሚያጠራ የደቡብ አፍሪቃ የሀቅ እና የእርቅ ኮሚሽን የተባለዉን አቋቋሙ። እ.ኤ.አ በ1999 ከፖለትካ ከተሰናበቱ በኋላ ማዲባ ለህብረተሰብ ጉዳዮች፤ ህፃናትን ለመርዳት እና የኤች/አይ/ቪ ኤድስ ህመምተኞችን በመርዳት ስራ ላይ ተሰማሩ። ማንዴላ ጠንካራ ጎን እንደነበረዉም ሁላ ደካማ ጎንም ነበረዉ። በኋላ ላይም በስልጣኑ ጊዜ ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ለማስቆም በቂ ስራ እንዳልሰራ አምኗል። በደቡብ አፍሪቃ ድህነትን ለመዋጋት የተደረገው ሙከራ ስኬታማ አለመሆኑም የማንዴላን ፖለቲካዊ ስራዎቹን አደብዝዘዋል።

የ17 ዓመቱ ወጣት ደቡብ አፍሪቃዊዉ ጋሞሌሎ  ቶቢሌ ማስዉኡ  ማንዴላ በማኅበረሰቡ ፍትህ እና እኩልነት ላይ በቂ ባለመስራቱ ተጠያቂ ያደርጓል፤ «እሱ ያደረገዉ ነገር በቂ ነበር፤ እሱ ተሟግቸላታለሁ የሚለዉ ሕዝብ ግን ፈጽሞ አላረካም።»

እንዲህ ዓይነቱ ትችት እንዳለ ሆኖ አሁንም የሱን ሥነ-ምግባር የተቀበሉት ብዙዎቹ ያደንቁታል። የ33 ዓመት ካሜሩናዊያ ፓሜላ ጌቹ የምከተለዉን ትላለች፤
«አመለካከቱ አድሎ የለለበት፤ እኩል መብትና ፍትህ እንድኖር ያደረገዉ ጥረት ለኔ ወሳኝ ቦታ አለዉ። ዓለምንም እንደት እንደሚመለከተ ይመራኛል። እኔ እንዲቋቋም የረዳሁት Coeur d'enfance ወይም «የልጅነት ጊዜ» የምለዉ ማህበር በሕብረተሰባችን ዉስጥ ያለዉን የእኩልነት እጦትና በሕፃናቶች መብት ላይ ይታገላል።»

ማንዴላ በህይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት  ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሰፋ ያለ ጊዜ ለማሳለፍ ከህዝብ አገልግሎት ርቀው ቁኑ ወደተባለችዉ  አነስተኛ መንደር ተመለሱ።
እ.ኤ.አ ታሕሣሥ 5 ቀን 2013 ኒልሰን ማንዴላ ሲሞቱ፤ ደቡብ አፍሪቃውያንን ጨምሮ መላው ዓለም አዘነ።  አሁንም ግን ብዙ ወጣት አፍሪቃውያን ማንዴላ በአሁኑ ጊዜ በአፍሪቃ ካሉት መሪዎች ጋር የሚወዳደሩ እንዳይደሉ ይናገራሉ። የላይቤርያ ዜግኔት ያላት ፓትርስ ጁሃ ይህን ከሚሉት አንዷ ናት፣ «ማንዴላ የአንድነት፤ የፍቅርና የድፍረት ተምሳሌት ናቸዉ። እሳቸዉ ህዝቡን የሥራቸው ማዕከል የሚያደርጉ የመጪዎቹን የአፍሪቃ መሪዎች ተግዳሮት ነው የሚወክሉት።»

ምስክርነቶችን እዚህ ይመልከቱ: http://www.dw.com/en/top-stories/nelson-mandela/s-100531

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ