1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ምክር ቤት ጉባኤ ተጠናቀቀ

ሰኞ፣ ጥቅምት 12 2011

የትግራይ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ካለፈው ቅዳሜ እስከ ዛሬ አካሄደ።  የሦስት ቀን ጉባኤ የተለያዩ አዋጆች እና ሹመቶችን አጽድቋል።

https://p.dw.com/p/36xZD
Tigray Parlament Kongress Neues Kabinett
ምስል DW/M. Haileselassie

አዋጆችን እና አዳዲስ ሹመቶችን አጽድቋል

 

ዛሬ የተጠናቀቀው የሦስት ቀኑ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ፤ አፈ ጉባኤውን አሰናብቶ የካቢኔሹም ሽር አድርጎ ዘጠኝ አዳዲስ ሰዎችን መሾሙም ተገልጿል።  በትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አቅራቢነት 9 የቢሮ ኃላፊዎችና 3 የዞን አስተዳዳሪዎች ምክር ቤቱ ሹመታቸው አፅድቋል፡፡ ከዘጠኙ አዳዲስ የካቢኔ አባላት መካከል 6 ሴቶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የቀድሞ የደህንነት ሐላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር የድህንነትና ፀጥታ አማካሪ ሆነዋል፡፡ ለ2011ዓ,ም የሚያከናውነውን እቅድ በማቅረብም አፀድቋል።  ከመቀሌ ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ