1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች  ጉባዔ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 10 2010

በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ 50 የኢትዮጵያውያን ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ የብሔራዊ መግባባት እና እርቀ ሰላም ጉባዔ አካሄዱ።

https://p.dw.com/p/33GxX
Äthiopien, Addis Abeba, Parteikonferenz der Opposition
ምስል DW/G.Tedla

ብሔራዊ መግባባት እና እርቀ ሰላም

በአዲስ አበባ የተደረገው ጉባዔ ዋና ዓላማ ገዢው ኢህአዴግ  ብቻውን መልስ ሊያገኝላቸው ላልቻላቸው  የሀገሪቱ ችግሮች ባንድነት በመወያየትr መፍትሔ የሚገኝበትን መንገድ ማፈላለግ እንደሆነ ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ መኢአድ ፕሬዚደንት ዶክተር በዛብህ ደምሴ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ከፈለጉ በመጀመሪያ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት ማስወገድ እንደሚገባቸው ተሳታፊዎች አስታውቀዋል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ